የከተማችን ህብረተሰብ ከምንም በላይ ለጤናው ቅድሚያ በመሥጠት ተመርምሮ ጤናማነቱ የተረጋገጠ ሥጋ ብቻ በመጠቀም ከሁለት መቶ በላይ ከሆኑ አደገኛ ተላላፊ በሽታዎች እራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ እያስገነዘብን፤ ለህብረተሰቡ ጤና ግድ የማይላቸውንና በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩ ህገ-ወጥ የሥጋ ነጋዴዎች ሲያጋጥሙት ለህግ አስከባሪ፤ ለጤና ቢሮ፤ ለአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጥቆማ እንዲያደርግ እያሳሰብን፤ ሀገራችን የነደፈችውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ እንድትሰለፍ መላው ህብረተሰብ ድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡