የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ተልእኮ ንፅህናውን የተጠበቀና ተመርምሮ ጤናማነቱ የተረጋገጠ የእንስሣት እርድ አገልግሎት በተወዳዳሪ ዋጋ ለአዲስ አበባ ከተማ ደንበኞቹ በቅልጥፍናና በታማኝነት መስጠትና ከተረፈ ሥጋ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸውን ምርቶች በጥራት በማምረት መሸጥ ነው፡፡ ድርጅቱ ይህንን ተልዕኮ ለማሳካት አሠራሩን ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት በመስጠት የድርጅቱን ትርፋማነት በከፍተኛ ደረጀ ለማሻሻልና ረጅም አመታት ሳይሻሻል የቆየውን ተቋም አሠራሩን በመቀየር ተቋማዊ ሽግግር በማድረግ መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ትግበራ ላይ ይገኛል፡፡