የጅማ ከተማ ምክር ቤት አባላት በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ!
የጉብኝቱ አላማ በዋነኝነት ከተቋሙ ልምድ ለመቅሰም እና በተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ጉብኝት ነው ሲሉ የምክር ቤት አባላቶቹ ገልፀዋል ፡፡
ድርጅቱ ለምግብነት የማይውል ተረፈ ስጋን ዘመናዊ ማሽኖችን በመጠቀም ወደ ምርትነት በመቀየር ለተጨማሪ የገቢ ምንጭነት ማዋል መቻሉ እጅግ ውጤታማ እና ለሌሎች ተቋማት በተለይም ለአጎራባች ቄራዎች እንደ ከፍተኛ ልምድ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡
ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም አንፃርም ተቋሙ ተሽከርካሪዎቹ ላይ የጂ.ፒ.ኤስ (GPS) ቴክኖሎጂን በመጠቀሙ የነዳጅ አጠቃቀሙን መቆጣጠርና በከፍተኛ ሁኔታ መቆጠብ መቻሉ ለሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት እንደ መልካም ተሞክሮ የሚወሰድመሆኑን አባላቶቹ ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ የአዲሰ አበባ ቄራዎች ድርጅት አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ተደገፈ ማድረግ መቻሉ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆንና እና በከፍተኛ ሁኔታ ልምድ ያገኘንበት ነው ሲሉ የምክር ቤት አባላቶቹ ጨምረው ገልፀዋል ፡፡