የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የአቢሲኒያ አዋርድ የመጀመሪያ ደረጃ ጥራት ስራ አመራር ዲፕሎማ ተሸላሚ ሆኑዋል
ሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም
አቢሲኒያ ሽልማት የሀገር ባለውለታ ተቋማትና ግለሰቦች ከፍተኛ ዲፕሎማ ፣ የወርቅ ሜዳልያና የኒሻንና የዋንጫ ሽልማት ሰጠ።
ይህ በሀገራችን በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተካሄደ የመጀመሪያው የሽልማት መርሀ ግብር ሲሆን ከ57ሺህ የኢንዱስትሪ ተቋማት ከተመረጡት 50 ተቋማት መካከል የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አንዱ በመሆን ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተዘጋጀው የሽልማት ላይ ከኢፌድሪ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እጅ ከፍተኛ ዲፕሎማ ዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
የሸልማቱ የተሸላሚዎች ምርጫ አገልግሎት አሰጣጣቸውና ምርታቸውን መሰረት በማድረግ በአጠቃላይ ተቋማዊ ውጤታቸው ላይ ከ2009-2014 በተደረገ ውጫዊ ምዘና በ24 መሰረታዊ መለኪያዎች አዳዲስና ዘመናዊ አሰራር የዘረጉ ተቋማት ፣ የላቀና ተጨባጭ/የሚታይ እድገት ላስመዘገቡ ተቋማት ፣ ለሰራተኞቻቸው ምቹ የስራ ስርአት የዘረጉ ተቋማት ፣ መልካም ስማቸውን ጠብቀው ለአመታት ለዘለቁ ተቋማት እና ለረጅም አመታት በትጋት ለሰሩ ተቋማት/BASED ON: MESIONE BRANDING AND REPUTATION/ ላይ ተመስርቶ በተገኘ ውጤት እንዲመረጡና እንዲሸለሙ መደረጉ ተገልፆዋል፡፡
የአቢሲኒያ ሽልማት ፈቃድ አግኝቶ ስራ በሚሰራባቸው የሸልማት መስኮች መሀከል የከፍተኛ ክብር ሽልማት ዋነኛው ነው::በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደው የሽልማት መርሀግብር ላይ የኢፌድሪ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደሁም ባለሃብቶች እና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተገኝተዋል።
ከተቋሙ በተጨማሪ በአገልግሎት ዘመናቸው ጥሩ አመራር በመሆን ድርጅቱን ላገለገሉ ሁለት የስራ አመራር አባላት እንዲሁም በተቋማችን ከሚገኙ የስራ ሂደቶች የተሻለ የስራ አፈፃፀም እና መልካም ስነ-ምግባር ያላቸው አምስት የድርጅቱ ሠራተኞች ምርጥ ሠራተኞች በሚል ዘርፍ የሜዳሊያ ሽልማት በእለቱ ተረክበዋል፡፡
ተሸላሚዎቹም ወ/ሮ ገነት በለጠ የእርድ አገልግሎትና የስጋ ስርጭት የስራ ሂደት ዳይሬክተር ፣ አቶ ጥበቡ ጥሩነህ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ ጌታቸው እሸቴ፣ አቶ ጌታቸው በቀለ፣ አቶ መላኩ አበበ፣ አቶ አፈወርቅ ቢራቱ እና አቶ ጌታሁን አባይነህ ሽልማታቸውን የአቢሲኒያ ሽልማት መስራችና ስራ አስኪያጅ ከሆኑት ከአቶ ግርማ በቀለ ፣የአቢሲኒያ የቦርድ ፕሬዝዳንት ሰብሳቢ ከአቶ አሰፋ ከሲቶ እና የኢትዮዽያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ከአቶ ካሳሁን ፎሎ እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡
በመጨረሻም ለተሸላሚ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም ለተሸላሚ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በቀጣይም የጥራት መለኪያ መስፈርቶችን በመጠቀም ጥራትን የድርጅታችን የአሰራር ባህል ማድረግ እንደሚገባም በሽልማት መድረኩ ተገልፆዋል፡፡