የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ምስጋና አቀረበ!
የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር እና የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ንፅህናውን የተጠበቀ ስጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ እና ተደራሽ ለማድረግ በአንድ ዓይነት አላማ ተቋቁመው የሚንቀሳቀሱ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ናቸው፡፡ በዚህም ለረጅም ዓመታት የዘለቀ የስራ ግንኙነትን በመፍጠር የከተማዋን ነዋሪዎች የስጋ ፍላጎት ለሟሟላት የበኩላቸዉን ድርሻ እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ ይህ ዘመን ተሻጋሪ የስራ ግንኙነት ከአመታት በኋላም ተጠናክሮ ቀጥሎ በዘንድሮዉ የአብይ ፆም ቅበላ ስራ የድርጅቱ ሃላፊዎች እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ባደረጉት የተቀናጀ ርብርብ ለከተማዉ ነዋሪ በእንስሳት ሃኪም የተመረመረና ጤንነቱ የተረጋገጠ የስጋ ምርት እንዲደርሰዉ ላሳያችሁት ተነሳሽነት እና የአመራር ሰጪነት ሚና ልኳንዳ ማህበሩ ላቅ ያለ ምስጋናዉን በማህበሩ የዳሬክተሮች ቦርድ ስም ያቀርባል በማለት በላከዉ የምስጋና ደብዳቤ አስታዉቋል፡፡