አዲስ የተሰየሙት የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ አባላት
የቀድሞ የድርጅቱ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው ስራቸውን አዲስ ለተሰየሙት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ማስረከባቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም አዲስ የተሰየሙት የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ አባላት በድርጅቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በመገኘት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አከናውነዋል፡፡ የጉብኝቱ ዋና አላማም ቀጣይ ስራዎችን በጋራ ለማከናወን አመቺ ይሆን ዘንድ የተቋሙን አሁናዊ ውስጣዊ እና ውጫዊ ይዘቶችን መገምገም እና ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ስለታመነበት መሆኑ በጉብኝቱ ተገልፆዋል፡፡