ዓለም አቀፍ የፀረ ኤች አይ ቪ /ኤድስ/ ቀን በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሰራተኞች ታስቦ ዋለ!
የዓለም ኤድስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በመከበር ላይ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሰራተኞች ‹‹ኤች አይ ቪን ለመግታት፣አለም አቀፋዊ ትብብር፣የጋራ ኃላፊነት››በሚል መሪ ቃል ዕለቱን በማሰብ በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄደዋል፡፡
በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀውን ሰነድ የድርጅቱ ክሊኒክ የጤና መኮንን የሆኑት አቶ አንተነህ ወንድምአገኘሁ ለተሳታፊዎች በንባብ አቅርበው አብራርተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም ኤች አይ ቪ/ኤድስ አሁንም የማኅበረሰብ ጤና ችግር ሆኖ መቀጠሉን ሁሉም ተገንዝቦ እያንዳንዱ ዜጋ ቅድመ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ምርመራ በማድረግና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል በማለት ገልፀው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች የምርመራና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ባለሙያው ገልፀዋል።