የደንበኞች እርካታ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥእየሰራ መሆኑን ድርጅቱ አስታወቀ።የድርጅቱ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጥበበ ጥሩነህ እንደገለፁት የደንበኞች እርካታ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥእየሰራ መሆኑን ና በዚህም መሰረት የጥሪ ማእከልና የደንበኞች ቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት ዘርግቶ ወደ ተግባር ለመግባት ዝግጅት መጨረሱን አያይዞ ገልፅዋል ይህ ተግባራዊ ሲሆን ደንበኞች በቀላሉ መረጃ ለመጠየቅ፤ቅሬታ ለማስመዝገብና የድርጅቱ ምርትና አገልግሎት ለማዘዝ እንደሚረዳ ዳይሬክተሩ ተናግርዋል ሲል የዘገበው የድርጅቱ ኢንፎርሜሽንና ህዝብ ግንኝነት አገልግሎት ነው፡፡