( በኢትዮ ኤፍ ኤም የቀረበ )
ዛሬ ማለዳ ጀምሮ በከተማዋ ያሉ ስጋ ቤቶች ከቄራ ድርጅት ውጪ እርድ እየተፈጸመ ለህብረተሰቡ እየተሸጡ ነው የሚል ጥቆማ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ስጋ ቤቶችን በመፈተሽ ላይ ይገኛል። እስካሁን በተደረገው አሰሳም ከፍተኛ መጠን ያለው ጤንነቱ ያልተረጋገጠ ስጋ ተገኝቷል።
በርካታ ስጋ ቤቶች አንድ በሬ በቄራዎች ድርጅት እርድ ካከናወኑ በኋላ በዚህ ሽፋን ተጨማሪ በሬዎችን ከቄራዎች ድርጅት እንደታረዱ በማስመሰል ህገወጥ ስጋ ለህብረተሰቡ ሊሸጡ በዝግጅት ላይ እያሉ በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
ይህ የተያዘው ህገወጥ ስጋም ከስጋቤቶቹ እንዲነሳ መደረጉን ነገር ግን የእንስሳት እርዶችን ከቄራዎች ድርጅት የፈጸሙ እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የቻሉ ግን ስራቸውን ቀጥለዋል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።