የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

ዜናዎች

የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መልካም አስተዳደር ለማስፈን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መልካም አስተዳደር ለማስፈንና የተገልጋዩን እርካታ ለማሟላት እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የስራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ጥበበ ጥሩነህ አስታወቁ፡፡

የድርጅቱን ስራዎች ፈጣንና ዘመናዊ ለማድረግ የICT ሲስተም ተግባራዊ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመቀነስና የቁጥጥር ስርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ  የደህንነት ካሜራ  /CCTV/ በተመረጡ 2 ቦታዎች ማለትም በሰዓት መቆጣጠሪያና በድርጅቱ መግቢያ በር ላይ ተተክለው ስራ መጀመራቸውን እና በ2012 ዓ.ም በድርጅቱ ውስጥ በተመረጡ 8 ቦታዎች በተጨማሪ እንደሚተከሉ ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም የድርጅቱን ተሽከርካሪዎች የነዳጅ አጠቃቀም ለመቆጣጠርና   ስምሪቱን ዘመናዊ ለማድረግ የ/GPS/ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊው ተለይቶ ለስራ አመራር ቦርድ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንና በተመሳሳይ ዘመናዊ የጥሪ ማእከል ግንባታ በጨረታ ሂደት ላይ መሆኑን በቅርብ ጊዜም ተግባራዊ እንደሚሆን ኃላፊው አያይዘው ገልፀዋል፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት