የልኳንዳ ባለቤቶች -በመስኩ (ተመሳሳይ) የንግድ ሥራ ፈቃድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ -የግብር መክፈያ ሠርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ -የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ -3x4 የሆነ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣ -የመመዝገቢያ ክፍያ መክፈል -ተወካይ ከሆኑ የውክልና ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ ለስጋ መሸጫ ሱቅ -የሥጋ መሸጫ ሱቁ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ መራቅ አለበት፣ -የመሸጫ ሱቁ በር፣መስኮት፣ከውስጥ ወለሉ ሲሾና ኮርኒስ ያለው፣ -የሱቁ ግድግዳዎች ከብሎኬት /ላሜራ/ የተሰራና ነጭ ቀለም የተቀባ መሆን አለበት -ለሥጋ መሸጫ የሚያሰፈልጉ መሣሪየዎች መከትከቻ፣ ቢላዋ፣ መክተፊያ፣ የእጅ መታጠቢያ፣ የስጋ መስቀያ ጋንቾች፣ አልባሳት ወ.ዘ.ተ መሟላት አለባቸው፣ -ሆቴሎችና ሬስቶራንቶች ከሆኑ የስጋ ማስቀመጫ ማቀዝቀዣ ፍሪጅ ሊኖር ይገባል፣ -ሥጋ ለማስገባት የተሽከርካሪ ማስገቢያና ማዞሪያ መንገድ ያለው፣ -ከዋናው መንገድ ከ15 ሜትር በላይ ያልራቀ፣ –የኤሌክትሪክና የስልክ ገመዶች ከተሽከርካሪ መተላለፊያ የራቁ መሆን አለባቸው፣ በአጠቃላይ ለከባድ መኪና ተሸከርካሪ መተላለፊያና በዞሪያ ወዘተ በቂ ቦታ መኖር አለበት |