የከተማችን ህብረተሰብ ከምንም በላይ ለጤናው ቅድሚያ በመሥጠት ተመርምሮ ጤናማነቱ የተረጋገጠ ሥጋ ብቻ በመጠቀም ከሁለት መቶ በላይ ከሆኑ አደገኛ ተላላፊ በሽታዎች እራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ እያስገነዘብን፤ ለህብረተሰቡ ጤና ግድ የማይላቸውንና በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩ ህገ-ወጥ የሥጋ ነጋዴዎች ሲያጋጥሙት ለህግ አስከባሪ፤ ለጤና ቢሮ፤ ለአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጥቆማ እንዲያደርግ እያሳሰብን፤ ሀገራችን የነደፈችውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ እንድትሰለፍ መላው ህብረተሰብ ድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
በየዕለቱ በሚኖረው ሂደት ውስጥ ለእርድ የሚሆኑ እንስሳትን ወደ ድርጅቱ በማምጣት ጤናማነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት ስጋ ለተጠቀሚዎቻቸው ለማቅረብ እርድ እንዲከናወንላቸው ያደርጋሉ
በተለያየ ምክንያት ለተለያዩ ዝግጅቶች የእርድ አገልግሎት የሚፈልጉ ደንበኞች አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ
የስጋና አጥንት፣ ሸሆና እንዲሁም ከተረፈ ምርት የሚገኙ ምርቶችን ለሌሎች ምርትበግብዓትነት ጥቅም ላይ ያውላሉ |
በእርድ ወቅት የሚሰበሰቡ የእንስሳት ቆዳና ሌጦዎችን ለቆዳ ምርት ውጤቶች እንደግብዓት ይጠቀማሉ
ታርደው ለደንበኞች ለሽያጭ የሚቀርቡ በጎችን ያቀርባሉ
በድርጅቱ ጤናማነቱ ተመርምሮ ለገበያ የቀረበ የበግ ስጋን በመግዛት ይጠቀማሉ
ከድርጅታችን የእርድ አገልግሎት በማግኘት ለደንበኞቻቸው ደረጃውን የጠበቀ የስጋ አቅርቦት ያከናውናሉ
Visit Today : 45 |
Visit Yesterday : 151 |
This Month : 1682 |
Total Visit : 35025 |