የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ኀዳር 12 ቀን 1949 ዓ.ም በአዋጅ የተቋቋመ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ሲሆን በተሰጠው ስልጣን መሠረት ጤናማነቱ በእንስሳት ሃኪም የተረጋገጠ የእርድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ ኀብረተሰብ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለኀብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተለያዩ የአሰራር ዘዴዎችን እየተጠቀመ በርካታ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው፡፡
ሆኖም ለኀብረተሰቡ በጥራትና በብቃት በመስራት የተሟላ እርካታ ከማስፈን አንፃር የድርጅቱ ሥራ በየወቅቱ የሚቀያየር በመሆኑ በርካታ ያልተወጣቸው ችግሮችና አጥረቶች እንዳሉ ከሚሰጠን ጥቆማና አስተያየት መረዳት ተችሏል፡፡